በምድረ በዳ ጎዳና አዘጋጁ

በምድረ በዳ ጎዳና አዘጋጁ

ዓለምን መለወጥ

አገልግሎታችን በግለሰብ፣ በቤተሰብ እና በዓለም ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ተብሎ በተዘጋጁ አምስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የተገነባ ነው፦

ያልተደረሰባቸውን መድረስ
እያንዳንዱ ሰው መለኮታዊ ዓላማውን እንዲያውቅ ለመርዳት የክርስቶስን ፍቅር እና የድነትን መልእክት ማወጅ።

ቅዱሳንን ማስታጠቅ

አማኞችን ወደ መንፈሳዊ ብስለት በመምራት ብቁ የመንግስቱ ዜጎች እንዲሆኑ ማስታጠቅ።

ግንኙነቶችን መገንባትና መንከባከብ
በክርስቶስ ጠንካራ ጋብቻዎችን እና ጥብቅ ግንኙነቶችን ለመገንባት አስፈላጊ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶችን እና ተግባራዊ አቅራቦቶችን ማቅረብ።

ሁሉንም ትውልድ ማጠንከር
ወንዶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ህፃናት ማንነታቸውን እንዲጨብጡ እና በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ያላቸውን ተገቢ ስፍራ እንዲይዙ የሚያስችሉ መድረኮችን መፍጠር።

ለምጻቱ መዘጋጀት
ፈጻሚውን ትውልድ እና በዓለም ዙሪያ ያለውን የክርስቶስ አካል ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ማጠንከር።

ጉዞአችን እና ዓለም አቀፋዊው ግንኙነት

የCongressWBN አባል

በ 1999 (EC) የተመሰረተው፣ የሌዋዊያን ኪንግደም ሴንተር በምስራቅ ስዊዘርላንድ የእምነት አምድ ማህበረሰብ ሆኖ ቆይቷል። እኛ ሕይወት በአንድነት በመካፈል የወንድማማችነት ባህልን ማዳበር፣ ቤተሰቦችን ማጠናከር እንዲሁም ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት ላይ እናተኩራለን
ከ120 በላይ ሀገራት ውስጥ በሚሠራ ኮንግረስ WBN ተብሎ በሚጠራው ልዩ ዓለም አቀፍ እምነት-ተኮር ድርጅት ውስጥ ዋና ማኅበረሰብ (Core Community) ሆነን ለማገልገል ቁርጠኞች ነን። በዶ/ር ኖኤል ዉድሮፍ ሃዋሪያዊ (Dr. Noel Woodroffe) አመራር ሥር፣ በሴንት ጋለን የሚገኘው የአካባቢያችን ማኅበረሰብ በምድር ላይ ለእግዚአብሔር አላማዎች ከሚተጉ አለም ኣቀፍ እንቅስቃሴ ጋር የሚያገናኝ የተለየ ጸጋ እንቀበላለን እናስተላልፋለን።

ዓለም አቀፋዊው ትስስራችን በተመለከተ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ:
www.congresswbn.org

በረከት ረታ

መድሃኔ መሃሪ

መብራህቱ ገብረማርያም

የአመራር ቡድን

መንፈሳዊ እረኞች

የሌዋዊያን መንግስታዊ ማዕከል የሚመራው ለማህበረሰቡ መንፈሳዊ ክትትል፣ ራዕይ እና አቅጣጫ ለማያሳየት በሚተጉ ቡድን ነው፡

በረከት ረታ – ዋናመ
መብራህቱ ገብረማርያም – ምክተል መሪ
መድሃኔ መሃሪ – ረዳት ስራ አስፈጻሚ (Executive Support Officer)

እነዚህ መሪዎች በሰፊ የአመራር ቡድን እየተደገፉ በአንድነት ምዕመናኑን ይንከባከባሉ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልዕኮ ወደፊት ለማስፋፋት አብረው ያገለግላሉ።

ቡድኖች

በእኛ ዘንድ እያንዳንዱ የእድሜ ደረጃ የራሱ ቦታ አለው። ቡድኖቻችን ልጆችን፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችን እና ወንዶችን በግል እድገታቸው፣ በእምነታቸው እና በእውነተኛ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲያድጉ ይረዱአቸዋል። ለእርስዎ የሚስማማውን ቡድን ያግኙ እና የቤተሰባችን አባል ይሁኑ።

PH

እስከ 11 ዓመት ዕድሜ ላሉ ህጻናት

Evolution

ከ12-14 ዓመት ዕድሜ ላሉ ወጣቶች

GPS

ከ16-21 ዓመት ዕድሜ ላሉ ወጣቶች

X-Elle

ከ21-39 ዓመት ዕድሜ ላሉ ሴቶች

Charis

40 ዓመት እና ከዚያ በላይ ላሉ ሴቶች

Hebron

21 ዓመት እና ከዚያ በላይ ላሉ ወንዶች

ጥያቄዎች?

እንግዲያውስ ያግኙን።
ለእርስዎ እዚህ ነን።